በኢትዮጵያ ግጭት የተሳተፉ የተለያዩ ወገኖች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ብለው እንደሚያምኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪዎች ዛሬ ገለጹ።
በትግራይ ክልል ሰብአዊነት ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች በስተጀርባ የመንግሥት እጅ እንዳለም ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን እንዲመረምር በመንግሥታቱ ድርጅት የተሰየመው የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ከጎርጎሪዮሳዊው 2020 ዓ.ም ጀምሮ በሀገሪቱ መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰት መፈጸሙን የሚያሳይ መረጃ ማግኘቱን የሚያሳይ የመጀመሪያ ዘገባውን ይፋ ማድረጉን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ከጄኔቫ ዘግቧል።
የባለሙያዎቹ ዘገባ አክሎም «በበርካታ አጋጣሚዎች ይህን ለማመን የሚያስችል በቂ ምክንያት እንዳለው» በመግለጽ እነዚህ ጥሰቶች የጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ደረጃ የያዙ ናቸው ማለቱንም የዜና ምንጩ ዘግቧል።
0 አስተያየቶች