Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሁሩ ኬንያታ ግጭቱን ለማስቆም ኢትዮጵያውያን እንዲወያዩ አሳሰቡ



የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ግጭቱን ለማስቆም ኢትዮጵያውያን እንዲወያዩ አሳሰቡ፡፡ 


ኬንያታ የኢትዮጵያ ተፋላሚ ወገኖች ድርድር ይጀምሩ ሲሉ ነው የጠየቁት፡፡ 


ህወሓት እና 'ኦነግ ሸኔ' የፌደራል መንግስቱን ለመውጋት ቅንጅት መፍጠራቸው ጦርነቱ ሌላ መልክ እንዲኖረው እና እንዲራዘም እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 


በፌደራል መንግስቱ እና በህወሃት መካከል እስካሁን ትርጉም ያለው ድርድር አለመጀመሩ ጦርነቱ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቀጥል አድርጎታልም ነው ኡሁሩ ያሉት፡፡ 


የኢትዮጵያ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ጦርነቱን ለማስቆም ድርድር እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡


ኬንያን ጨምሮ አፍሪካ እና ዓለም ሰላማዊ ኢትዮጵያን ማየት ይፈልጋል ብለዋል ፕሬዝዳንት ኡሁሩ። 


አክለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተመካክሮ ለአገሩ ሰላም መፍትሄ እንዲፈልግ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ 


ኬንያታ ባሳለፍነው ወርሃ መስከረም ተካሂዶ በነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ ተገኝተው እንደነበር ይታወሳል፡፡ 



ከሳምንት በፊት ወደ አሜሪካ አቀንተው ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በኢትዮጵያ እና ሌሎች ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውም አይዘነጋም፡፡ 



አሜሪካም የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋን አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማንን ወደ ኢትዮጵያ እንደምትልክ አስታውቃለች፡፡ 


ልዩ መልዕከተኛው ዛሬ ሃሙስ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ/ም ለሁለት ቀናት ጉብኝት አዲስ አበባ እንደሚገቡም ይጠበቃል፡፡ 


ከ10 ቀናት በፊት ሱዳን የነበሩት ፌልትማን ከአሁን ቀደም በኢትዮጵያ እና በኬንያ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል ሲል የዘገበው አል ዐይን ነው፡፡

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች