Ticker

6/recent/ticker-posts

አርጀንቲናዊት እንስት ያለ ምንም መድኃኒት ከኤችአይቪ ዳነች



መኖሪያዋን በአርጀንቲና ያደረገች ሴት ያለ ምንም ዓይነት መድኃኒት ከኤችአይቪ ኤድስ መዳኗ ተገልጿል። 


ከዚህ በፊት አንድ ግለሰብ እንዲሁ ያለመድኃኒት ከበሽታው ድኖ ነበር። 


ከቢሊዮን በላይ የደም ህዋሳቷ ላይ ምርመራ ተደርጎ ኤችአይቪ የሚባል ቫይረስ ቅንጣት ሊገኝ አልቻለም ሲል አርካይቭስ ኦፍ ኢንተርናል ሜዲሲን ዘግቧል። 


ግለሰቧ እንዴት ከኤችአይቪ እንደዳነች ማወቅ ቢቻል በሽታውን ከምድረ ገጽ ማጥፋት ይቻል ነበር ይላሉ የዘርፉ ሰዎች። 


ዶክተሮች በሴትዬዋ የደም ህዋሳት ላይ ያደረጉት ጥናት የሚያሳየው አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሮ ኤችአይቪን መከላከል የሚችል አቅም እንደተለገሳቸው ነው። 


የተወሰኑ ሰዎች በሽታው ወደ ሰውነታቸው እንዳይዘልቅ የሚያደርግ የዘር ቅንጣት አላቸው። 


"ኢስፔራንዛ" የተባለው ማንነቱ እንዳይታወቅ የሚፈልግ ግለሰብና ሌሎች ደግሞ ቫይረሱ ቢይዛቸውም ቀስ በቀስ በራሱ ጊዜ ይለቃቸዋል። 


ነገር ግን አብዛኛዎቹ በኤችአይቪ የሚያዙ ሰዎች ለሕይወት ዘመን የሚቆይ እንክብካቤ ይሻሉ። 


መድኃኒት መውሰድ ካቆሙ ሰውነታቸው ውስጥ ያለው ቫይረስ ያገግምና በጤናቸው ላይ እንደ አዲስ ችግር ሊያስከትል ይችላል። 


በቅርብ ዓመታት አንዳንድ ሰዎች ምንም ዓይነት መድኃኒት ሳይወስዱ ነገር ግን የተወሰነ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ቫይረሱን መቆጣጠር እንደሚችሉ ተደርሶበታል። 


አዳም ካስቲሌሆ የተሰኘው ሎንዶን የሚኖር ግለሰብ የኤችአይቪ እንዲሁም የካንሰር በሽታ ተጠቂ ነው። ለካንሰር ሕክምና ከለጋሽ የደም ህዋስ ካገኘ በኋላ ግን የኤችአይቪ መድኃኒት መውሰድ አቁሟል። 


የካንሰር ሕክምና እያገኘ ባለበት ወቅት ኤችአይቪ ያለባቸው የደም ህዋሳቱ ተጠራርገው ጠፍተዋል። 


ጉዳዩ ሲጣራ የደም ህዋስ የለገሰው ግለሰብ በዓለማችን ካሉ አንድ በመቶ ኤችአይቪን መከላከል ከሚችሉ ሰዎች መካከል መሆኑ ተደርሶበታል። 


የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ጆን ፍራተር በበኩላቸው አርጀንቲናዊቷ ብቻ ሳትሆን ሌሎችም ሰዎች መሰል አቅም ሊኖራቸው ስለሚችል ጥናት ማድረግ ያሻሉ ይላሉ። 


የራጎን ማሳቹሴትስ ጄኔራል ሆስፒታል ዶክተር የሆኑት እንዲሁም የዚህን ጉዳይ ጥናት የሚመሩት ዶ/ር ዙ ዩ ይህንን ሂደት በተፈጥሮ ቫይረሱን ማጥፋት ለማይችሉ ሰዎች ማስተላለፍ የሚቻልበት መላ ይኖራል ይላሉ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። 


ዶክተሩ እንደሚሉት ዕድሜ ልካቸውን መድኃኒት የሚወስዱ ሰዎች በክትባት መልክ የሰወነት መከላከል አቅማቸው እንዲዳብር ተደርጎ ያለመድኃኒት ከቫይረሱ ጋር መኖር እንዲችሉ ለማድረግ ዕቅድ አለ።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች