Ticker

6/recent/ticker-posts

የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ከተፈለገ፤ የህወሓት ኃይሎች ሶስት ቅድመ ሁኔታዎችን ሊያሟሉ ይገባል- ዲና ሙፍቲ



አንድ ዓመት ያስቆጠረውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ከተፈለገ፤ የህወሓት ኃይሎች ሶስት ቅድመ ሁኔታዎችን ሊያሟሉ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ አስታወቁ። ቅድመ ሁኔታዎቹ፤ የህወሓት ኃይሎች ጥቃት እንዲያቆሙ፣ ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲወጡ እንዲሁም የፌደራል መንግስቱን ህጋዊነት እንዲቀበሉ የሚጠይቁ ናቸው። 


ቅድመ ሁኔታዎቹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴን እና የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፤ ለውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች ባለፈው ሳምንት ማሳወቃቸውን አቶ ዲና ተናግረዋል። ሁለቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ስለ ቅደመ ሁኔታዎቹ የተናገሩት፤ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ማብራራያ በሰጡበት ወቅት ነው።   


ባለስልጣናቱ “በጁንታው የተፈጠሩ የሰላም እንቅፋቶች በሙሉ መነሳት እንዳለባቸው፤ ይሄ እስከሆነ ድረስ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ለሰላም ምንጊዜም ዝግጁነቱ እንዳለ” ለዲፕሎማቶቹ እንዳብራሩ አቶ ዲና ገልጸዋል። በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ያለው የሰላም ዝግጁነት “ከአንዴም ሁለቴ በግልጽ ታይቷል” ያሉት ቃል አቃባዩ፤ ለዚህም የፌደራል መንግስት የተናጥል ተኩስ አድርጎ ከትግራይ የወጣበትን ሁነት ለማሳያነት ጠቅሰዋል። 

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች