ፓርላማው የ22 ሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን ሹመት አጸደቀ
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ረቡዕ ዕለት ባካሄደው በ6ኛ ዙር 1ኛ አመት 1ኛ ልዩ ስብሰባው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያቀረቡትን የአዲሱን መንግሥት 22 የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ሹመት አጽድቋል። ሹመቱ የጸደቀው በሁለት ተቃውሞና በ12 ድምጸ ተዐቅቦ ነው። ከመካከላቸው ሦስቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ባለሥልጣናት ናቸው። ተሿሚ ሚኒስትሮቹም ዛሬ በምክር ቤቱ ቃለ መሀላ ፈጽመዋል ። ምክር ቤቱ ሹመታቸውን አጽድቆላቸው ቃለ መሀላ የፈጸሙት የአዲሱ ካቢኔ አባላት
1. አቶ ደመቀ መኮንን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
2. ዶ/ር አብርሃም በላይ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር
3. አቶ አህመድ ሽዴ የገንዘብ ሚኒስትር
4. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የስራና ክህሎት ሚኒስትር
5. አቶ ኡመር ሁሴን የግብርና ሚኒስትር
6. ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር
7. ዶ/ር ኢንጀነር ሃብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
8. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንገር የትምህርት ሚኒስትር
9. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ- የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስትር
10. አቶ ገ/መስቀል ጫላ የንግድና እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር
11. አቶ መላኩ አለበል የኢንደስትሪ ሚኒስትር
12. አቶ ብናልፍ አንዱዓለም አሸናፊ የሰላም ሚኒስትር
13. ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የፍትህ ሚኒስትር
14. ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር
15. አቶ በለጠ ሞላ ጌታሁን- የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
16. አምባሳደር ናኒሴ ጫሌ- የቱሪዝም ሚኒስትር
17. አቶ ላቀ አያሌው- የገቢዎች ሚኒስትር
18. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ኢብራሂም-የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
19. ታከለ ኡማ በንቲ- የማዕድን ሚኒስትር
20. ዶ/ር ፍፁም አሰፋ- የፕላን ልማት ሚኒስትር
21. ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ-የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
22. ቀጀላ መርዳሳ -የባህልና ስፖርት ሚኒስትር
ናቸው።
ከመካከላቸው ሦስቱ ከብልጽግና ፓርቲ ውጭ ሲሆኑ እነርሱም ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ መሪ፣ አቶ በለጠ ሞላ ጌታሁን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ሊቀመንበር እንዲሁም አቶ ቀጀላ መርዳሳ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ምክትል ሊቀመንበር ናቸው። ምክር ቤቱ የሚኒስትሮቹን ሹመት ከመቀበሉ በፊት የፌዴራል መንግስት የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባርን መወሰኛ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።
ፎቶ፦ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
ምንም አስተያየቶች የሉም