ደመቀ መኮንን እና አንቶኒዮ ጉተሬዝ በትግራይ ቀውስና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ተወያዩ
የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከየተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በኒውዮርክ ተወያዩ።
በኒውዮርክ የተመድ ስብሰባ እየተካፈሉ የሚገኙት ደመቀ መኮንን፤ ከሀገራት ባለስልጣናት እና ከተቋማት አመራሮች ጋር የጎንዮሽ ምክክር እያደረጉ ነው። በትላንትናው ዕለትም ከዋና ፀሐፊው ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር መክረዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣው መረጃ ዋና ፀሐፊው እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
ዋና ፀሐፊው ወደ ሰላም የሚወስዱ ሂደቶች እንዲኖሩ በድጋሚ ጥሪ በማቅረብ የሰብአዊ ተደራሽነትን ይበልጥ ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በሌላ በኩል የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ ዋና ፀሐፊው ውይይቱን እንደገና ማስጀመርን አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝበው ድርጅቱ ለአፍሪካ ህብረት ጥረቶች ድጋፉን እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።
Post Comment
ምንም አስተያየቶች የሉም