የጉራጌ ዞን ም/ቤት የክላስተር አደረጃጀትን ሳይቀበለው ቀርቷል።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በጉራጌ ዞን ዋና የቀረበው በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሐሳብ በአብልጫ ድምፅ ውድቅ ተደረገ።
የጉራጌ ዞን ባካሄደው 4ተኛ ዙር 8ኛ አመት 9ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ መሐመድ ጀማል የቀረበው ምክረ ሀሳብ በምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኃላ በ40 ድጋፍ በ52 ተቃውሞ የውሳኔ ሀሳቡ ውድቅ አድርጓል።
በውይይቱ የዞኑ ህዝብ በምክርቤቱ ያፀደቀው ህገመንግስታዊ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ ሊያይ ይገባል በሚል ምክርቤቱ በአብላጫ ድምፅ የክላስተር ውሳኔ ምክረሀሳብ ውድቅ አድርጓል።
0 አስተያየቶች