Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከሰሃራ በታክ ካሉ ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች



ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር  ከሰሃራ በታክ ካሉ ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች


የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲ ፒ ጄ) በአውሮፓውያኑ በ2021 ሪፖርቱ እስከ ኅዳር ወር መጀመሪያ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በመላው ዓለም 293 ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ እና ከእነዚህ ውስጥም 14 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸውንና ይህም ተቋሙ መረጃው ማጠናቀር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛው ቁጥር መሆኑ አስታወቀ።



ቻይና ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በጋዜጠኞች እስር አንደኛ ሆ የቆየች ሲሆን በተገባደደው የፈረንጆች ዓመትም 50 ጋዜጠኞችን በማሰር ቀዳሚውን ቦታ ይዛለች። ምያንማር፣ ግብፅ እና ቬትናም ቻይናን ይከተላሉ።


በመቀጠልም ቱርክ፣ ኤርትራ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሩሲያ እና ኢራን እያንዳንዳቸው በርካታ ጋዜጠኞችን አስረዋል  ሲል ሲፒጄ በሪፖርቱ ላይ አትቷል።



ሲፒጄ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ከሰሃራ በታች ጋዜጠኞችን በማሰር የቀዳሚነቱን ስፍራ ያያዘችው ኤርትራ ናት። 


ኢትዮጵያም በአሁኑ ሰዓት ዘጠኝ ጋዜጠኞችን በማሰር ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀመጧታል። 


ሜክሲኮ እና ህንድ በርካታ ጋዜጠኞች የተገደሉባቸዉ ሀገራት ናቸው። በህንድ አራት ጋዜጠኞች ሲገደሉ ሦስቱ በሜክሲኮ ተገድለዋል።

አስተያየት ይለጥፉ

0 አስተያየቶች