አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በበርሊን ማራቶን ቀድሞ ያሰበውን ሳያሳካ የቀረው በጤና ጉዳይ እና በአየር ንብረት ምክንያት መሆኑን ተናገረ።አትሌት ቀነኒሳ ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ለመስበር አቅዶ የነበረ ቢሆንም ውድድሩን ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል።ቀነኒሳ ከሁለት ዓመት በፊት እአአ 2019 በተካሄደው የበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ለመሻሻል ሁለት ሰኮንዶች ብቻ ቀርተውት ውድድሩን ማሸነፉ ይታወሳል።
ምንም አስተያየቶች የሉም