Latest

ads header

ዜና

በሰሜን ሸዋ እግር አልባ የበግ ግልገል ተወለደች



በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር በሚባል ወረዳ እግር የሌላት የበግ ግልገል መወለዷ ተሰምቷል፡፡ 


ፋና እንደዘገበው በወረዳው ጉርሜ በተባለ ቀበሌ ነው  ሴት የበግ ግልገሏ እግር አልባ ሆና የተወለደቺው። 


የወረዳው መንግሥት ኮምዩንኬሽን ፅህፈት ቤት ሀላፊ  ሽፈራ ለማ እንዳሉት አሁን ላይ ግልገሏ በመልካም ጤንነት ላይ ሆና ባለቤቶቹ  እየተንከባከቧት ይገኛሉ። 



በሳይንሱ እዲህ አይነት አፈጣጠር ይከሰታል ያሉት በሰሜን ሸዋ ዞን እንሰሳት ሀብት ተጠሪ ፅህፈት ቤት የእስሳት በሽታ ቅኝት ባለሙያ  ዘላለም ይታየው መንስዔው በትክክል ይህ ነው ባይባልም በእርግዝናዎቹ የመጀመሪያ 36 ሰዓታት በተወሰደ መድሃኒት አልያም  ከእናትና አባት በተቀበለችው ጅን ምክንያት ሊከሰት ይችላል ነው ያሉት። 


በጎቹ ከሚመገቡት መኖ ጋር ኬሚካል ከተመገቡም ይህን አይነት ፍጥረት ሊገጥም ይችላል ብለዋል። 


ባለሙያው  በዞኑ ከዚህ በፊት 5 እግሮች ያሏት በግ መወለዷን አስታውሰዋል፡፡





ምንም አስተያየቶች የሉም